Hiyaw Tesfa

ለውድ ወንድማችን/እህታችን-­­­­­ _____________________________

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰህ/ሽ!

 የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ሰው ሆኖ ወደ ምድር መምጣትና መወለድ ስናስብ ለመሆኑ ምን ይሰማናል? ብዙ ሰዎች ይህን የጌታ ልደት መታሰቢያ በዓል የመብልና የመጠጥ በዓል ያደርጉታል፡፡ ለምን አምላክ የሆነው ጌታ ሰው ሆኖ በዝቅተኛ ሥፍራ እንደተወለደ አይገነዘቡም፣ አንተስ/ አንቺስ? ጌታ ክርስቶስ በተወለደበት ጊዜ መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ ለነበሩ እረኞች የተገለጠውና የጌታን የመወለድ የምስራች ያበሰረው መልአክ የተናገረውን ከመጽሐፍ ቅዱስ ልብ እንበል፡፡

“እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ።

መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤

ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና” (ሉቃ. 2፡10-11)

ከዚህ ጥቅስ እንደምንገነዘበው ጌታ የተወለደውና ሰው የሆነው ለሕዝቡ ሁሉ (ለእኔ፣ ለአንተ፣ ለአንቺ) መድኃኒት ለመሆን ነው፡፡ ትክክለኛ መድኃኒት ለበሽታ ፈውስ ይሆናል፣ ከሞትም ይታደጋል፡፡ እኛ የሰው ልጆች ሁሉ የኃጢአት በሽታ አለብን ይህ በሽታ ደግሞ ከዘላለሙ አምላክ ከእግዚአብሔር ለይቶናል፣ መድኃኒቱን ካላገኘን ወደ ሞት ያሻግረናል፡፡ ከኃጢአት በሽታና ከዘላለም ሞት የሰውን ልጅ ሁሉ መታደግ የሚችል መድኒት በምድር ላይ አልተገኘም፣ ወደፊትም አይገኝም፣ ብቸኛው መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው! ለዚህም ነው ኢየሱስ ያድናል የምንለው፡፡ ሕፃኑን ኢየሱስን በሕጋቸው መሠረት ታቅፈው ወደ ቤተመቅደስ በወሰዱት ጊዜ ፃድቅና ትጉህ የነበረው ስምዖን የሚባል ሰው የኢየሱስን መወለድ በዓይኑ አይቶ የተናገረውን አሁንም ከመጽሐፍ ቅዱስ እንመልከት!

“ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና፤

ይህም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን ለሕዝብህም ለእስራኤል ክብር ነው” (ሉቃ፣ 2፡31-32)፡፡

የኢየሱስ መወለድ፣ በሞት ጥላ ሥር ላሉት ሁሉ ሕይወት ነው፣ በጨለማ ላሉት ሁሉ ብርሃን ነው፡፡ ውድ ወንድማችን/እህታችን! ለአንተ/ለአንቺ የኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ ምንድነው? የዘላለም ሕይወት መድኃኒትና፣ ብርሃን የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በአንተ/በአንቺ ሕይወትና ኑሮ ውስጥ አለን? ከሌለ በሞት አደጋ ውስጥ ነህ/ነሽ! ለዚያውም የዘላለም ሞት! ዛሬውኑ አምልጥና/አምልጭና ወደ አዳኙ ጌታ ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ ና/ነይ! ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምንም ዓይነት የሚያድን መንገድ የለም! ነገ የአንተ/የአንቺ አይደለም! ዛሬውኑ ወስን/ወስኚ! ኢየሱስ ያድናል!!

Administrator

በአዳነ ደቻሣ

0911- 43- 6941 This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it   

ግብረሰዶማዊነትና ቤተክርስቲያን

የግብረሰዶማዊነት ጽንሰ ሀሳብ ሰለጠነ በተባለው ዓለም ወደ ኅበረተሰቡ እየሰረጸና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ፤ ቤተክርስቲያንም ለዚህ ጉዳይ አዎንታዊ ምላሽ እንድትሰጥ የጉዳዩ አቀንቃኞች በቤተክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ጫና በማሳደር ላይ ይገኛሉ፡፡ ጫና ማሳደር ብቻ ሳይሆን ጉዳዩ መጽሐፍ ቅዱሳዊና እግዚአብሔርም የተቀበለው እንደሆነ ለማረጋገጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ያጣቅሳሉ፡፡ በአሜሪካና በአዉሮፓ በመንግስት ዕውቅና የተሰጣቸው በርካታ የግብረሰዶማውያን ማህበራት መኖራቸው እሙን ነው፡፡ በአውሮፓ ውስጥ ከፍተኛ ዕውቅናና ተቀባይነት ያላት የአንግሊካን ቤተክርስቲያን ተመሳሳይ ጾታን ማጋባቷና ዕውቅና መስጠቷ የሩቅ ጊዜ ታሪክ አይደለም፡፡

 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገራችን ኢትዮጵያ ግብረሰዶማውያኑ ዕውቅና እንዲሰጣቸው ጥረት ማድረጋቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ከዚህም በላይ ደግሞ ወጣት ወንዶችና ተማሪዎች ተጠለፉና ተደፈሩ የሚሉ ዜናዎችንም በተለያዩ የመገናኛ አውታሮች በኩል መስማት ከጀመርን ውለን አድረናል፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ የሕዝቧ ማህበራዊ፣ ሞራላዊና ሥነ-ምግባራዊ ሁኔታ አንፃራዊ በሆነ መልኩም ቢሆን ጥሩ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ለዚህም ደግሞ ቤተክርስቲያን ከፍተኛውን አስተዋጽኦ እንዳደረገች እሙን ነው፡፡ ዛሬም ሕዝባችንን ከማህበራዊና ሞራላዊ ዝቅጠትና ቀውስ ለመታደግ መጽሐፍ ቅዱስን መመሪያዋ ያደረገች ትክክለኛዋ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ድርሻና ኃላፊነት አለባት፡፡

በዚህ አጭር ጽሑፌ የእግዚአብሔር ቃልና የቤተክርስቲያን ዋነኛ መመሪያ የሆነው፣ የሰውንም ሕይወት በመለወጥ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ታላቁ መጽሐፍ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ከብሉይ እስከ አዲስ ኪዳን ድረስ ስለ ግብረሰዶምና ስለግብረሰዶማውያኑ ምን እንደሚል እንዲሁም ደግሞ ትክክለኛዋ ቤተክርስቲያን በጉዳዩ ሊኖራት የሚገባውን አቋም በጥቂቱ ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡ ለዚህ ጽሑፌ የምጠቀመው መጽሐፍ ቅዱስ በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር አሳታሚነት በ 1954 ዓ.ም. በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት የታተመውን በተለምዶ ²አሮጌው² ወይም የ²ድሮው² ተብሎ የሚታወቀውን መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ይህን የመረጥኩበት አጭር ምክንያት በብዙ ኢትዮጵያውያን እጅ ስለሚገኝ ነው፡፡ ወደ ዋናው ጉዳይ እንግባ!

1.  ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 19

የዚህን ምዕራፍ ታሪክ ስንመለከት ሎጥ በሰዶም ይኖር በነበረ ጊዜ ሁለት መላእክት/ሰዎች ወደ ሰዶም ገቡ፤ ሎጥ ደግሞ በጥሩ የእንግዳ ተቀባይነት ባህሪው እነዚህን ሰዎች ይቀበላል፤ ወደ ቤቱም ያስገባቸውና ጥሩ መስተንግዶም ያደርግላቸዋል፡፡ እነዚህ መላእክቶች/ሰዎች ወደ ሎጥ ቤት መግባታቸውን ያዩ የከተማይቱ ሰዎች በዚያ ምሽት የሎጥን ቤት ከከበቡ በኃላ በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸዉ ? እናውቃቸው (ሩካቤ ሥጋ እንፈጽምባቸው) ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው (ቁ.5)፤ ብለው ሲያስጨንቁት ሎጥ ደግሞ ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ… ወንድ ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁ እንደወደዳችሁም አድርጓቸውብሎ ሲለምናቸው እናነባለን፡፡ ከዚያም ሰዎቹ የሎጥን ተማጽኖ እምቢ ብለው ቤቱን ሰብረው ለመግባት መታገላቸውን ከታሪኩ እንገነዘባለን፡፡ ከዚያ በኃላ የተከሰተውን በትኩረት ስንመለከት፡-

Ø  መላእክቱ/ሰዎቹ ሎጥን ወደ ቤት በማስገባት ከሰዶም ሰዎች አዳኑት፣

Ø  በቤቱ ደጃፍ የነበሩትን ሰዶማውያን ዓይናቸውን አሳወሩአቸው፣

Ø  ሎጥና ቤተሰቦቹ ከከተማይቱ በፍጥነት እንዲወጡ አደረጓቸው፣

Ø  በሰዶማዉያኑ ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ተቀሰቀሰ፣

Ø  እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፤

Ø  እግዚአብሔር ከተሞችን፣ በዙርያቸው ያለውንም ሁሉ፣ በከተሞቹ የሚኖሩትን ሁሉ፣ የምድሩንም ቡቃያ ሁሉ ገለበጠ (አጠፋ)፡፡

ከዚህ ጥቅስ ጠቅለል ባለ መልኩ የምንማረው፤ ግብረሰዶማዊነት እጅግ ክፉ ተግባር መሆኑን፣ የእግዚአብሔርን ቁጣ የሚቀሰቅስ መሆኑን፣ በጥቂት ግለሰቦች ክፉ ስራ በሕዝብና በአገር ላይ ሁሉ ከበድ ያለ ፍርድ የሚያመጣ፣ አገርንና ሕዝብን ለታላቅ ጥፋት የሚዳርግ አስጸያፊ ተግባር መሆኑን ነው፡፡

2.  ኦሪት ዘሌዋውያን ምዕ. 18፡22 እና ምዕ. 20፡13

ለእስራኤላውያኑ ማህበራዊና ሃይማኖታዊ መተዳደሪያ ሕግ በሙሴ በኩል ከእግዚአብሔር ተሰጥቶአቸዋል፡፡ በእነዚህ ጥቅሶች በቀጥታ ግብረሰዶማዊነትን የሚፃረር ሕገ እግዚአብሔር ከእግዚአብሔር ተሰጥቶአቸዋል፡፡ ጥቅሶቹን በቀጥታ እንመልከት፡-

Ø  ‹‹ከሴትም ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ ጸያፍ ነገር ነውና››(18፡22)፡፡

Ø  ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል ፈጽመው ይገደሉ ደማቸው በላያቸው ነው(20፡13)፡፡

ይህ ሕግ ለእስራኤላውያኑ ብቻ የተሰጠ ሳይሆን ዛሬም መጽሐፍ ቅዱስን ዋነኛ መመሪያ ላደረገችው ቤተክርስቲያንም ሆነ የሕይወታቸውና የኑሮአቸው መመሪያ ላደረጉ አማኞች ሁሉ የሚሠራ ነው፡፡ ስለሆነም በእግዚአብሔርና በሰውም ፊት ጸያፍ ከሆነውና ከባድ ፍርድን ከሚያስከትለው የግብረሰዶማዊነት ተግባር፣ አገርና ሕዝብ እንዲጠበቅ ቤተክርስቲያን ድርሻዋን ልትወጣ ይገባል፡፡

3.  ሮሜ ምዕ. 1፡18-32

ወደ አዲስ ኪዳን ስንሻገር ደግሞ የሮሜ መልዕክት ጸሀፊ የእግዚአብሔር ቁጣ በሰዎች ላይ የሚገለጥባቸውን ዋና ዋና መንፈሳዊና ማህበራዊ ምክንያቶች በተጠቀሰው ክፍል ዘርዝሮአል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ግብረሰዶማዊነት ነው፡፡ ጥቅሶችን በቀጥታ እንመልከት፡-

ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤…ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤

እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ።እንደነዚህ ለሚያደርጉት ሞት ይገባቸዋል የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ እነዚህን ከሚያደርጉ ጋር ይስማማሉ እንጂ አድራጊዎች ብቻ አይደሉም(ሮሜ 1፡24፤26-27፤32)፡፡

እንግዲህ ከዚህ ክፍል በግልጽ እንደምንረዳው ግብረሰዶማዊነት ተፈጥሮአዊ ባሕርይ አይደለም፡፡ የእግዚአብሔርን ተፈጥሮአዊ ሕግ የሚጥስ፣ ርኩሰት የተሞላበት አስነዋሪ ተግባርና ከእግዚአብሔር ዘንድ ቁጣንና ፍርድን የሚያመጣ ተግባር ነው፡፡ ስለሆነም እንደዚህ ዓይነት ተግባር ከሚፈጽሙ ጋር አብሮ መፈጸም ቀርቶ ከሀሳባቸው ጋር እንኳ መስማማት በእግዚአብሔር ፈጽሞ የተከለከለ ስለሆነ ትክክለኛዋ ቤተክርስቲያን በምንም መንገድ ይህን ተግባር እንደ ሰዎች መብትና ነጻነት አድርጋ ልትቀበል አይገባም፡፡

4.  1ቆሮንቶስ ምዕ. 6፡9-10

ማህበራዊ ሞራላዊና ስነ-ምግባራዊ ችግር ለገጠማት የቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን ሐዋሪያው ጳዉሎስ ከእግዚአብሔር መንግስት የሚያስቀሩ በርካታ ኃጢአቶችን ይዘረዝራል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱና የሰውን ልጅ አመጸኝነት አጉልቶ የሚያሳየው የግብረሰዶማዊነት ኃጥአት ነው፡፡ የሚከተለው ጥቅስ ይህንን እውነት በግልጽ ያስረዳናል፡፡

ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ

ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም(1ቆሮ.6፡9-10)።

የትክክለኛዋ ቤተክርስቲያን ትልቁ ተልዕኮ ለሰው ሁሉ የምስራቹን ወንጌል በመስበክ ሰዎች በክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀው የመንግስቱ ወራሾች እንዲሆኑ ማብቃት ነው፡፡ ስለሆነም የሰው ልጅን ከእግዚአብሔር መንግስት ከሚያስቀሩት አንዱና ዋነኛ የሆነውን የግብረሰዶማዊነትን ኃጢአት ትክክለኛዋ ቤተክርስቲያን አጥብቃ ልትዋጋ ይገባል፡፡

5.  1ኛ ጢሞቴዎስ ምዕ. 1፡9-11

ሐዋሪያው ጳውሎስ በዚህ መልዕክቱ፣ ሕግ የተሰጠበትን ዓላማ በመግለጽ ሐሰተኞች አስተማሪዎችን ወይም ደህና (መልካም) የሆነውን የወንጌል ትምህርት የሚቃወሙትን ሰዎች ባሕርይ ከማመልከቱም በላይ ሕግ የተሰጠበትን ዓላማ ያሳየናል፡፡ ጥቅሱን ልብ እንበል!

‹‹ይኸውም፥ ለበደለኞችና ለማይታዘዙ፥ ለዓመጸኞችና ለኃጢአተኞች፥ ቅድስና ለሌላቸውና ለርኵሳን፥ አባትና እናትን ለሚገድሉ፥ ለነፍሰ ገዳዮችና ለሴሰኞች፥ ከወንድ ጋርም ለሚተኙ፥ በሰዎችም ለሚነግዱ፥ ለውሸተኞችም በውሸትም ለሚምሉ፥ የብሩክ እግዚአብሔርንም ክብር እንደሚገልጥ ለእኔ አደራ እንደ ተሰጠኝ ወንጌል የሆነውን ደኅና ትምህርት ለሚቃወም ለሌላ ነገር ሁሉ ሕግ እንደ ተሰራ እንጂ ለጻድቅ እንዳልተሰራ ሲያውቅ ነው››(1ጢሞ. 1፡9-11)።

ስለሆነም እነዚህ ሰዎች ኅብረተሰባችንና ትውልዱን እንዳይበክሉ በፍቅርና በማቅናት አልያም በሕግ መጠበቅ ሀገራዊም፤ ክርሲቲያናዊም ግደታ እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል፡፡

6.  2 ጴጥሮስ ምዕ. 2፡2-10

ሐዋሪያው ጴጥሮስ ለሚጽፍላቸው ሰዎች አስቀድሞም ሆነ አሁን በሕዝቡ መካከል ሐሰተኞች ነቢያት እንደነበሩና እንዳሉ ከገለጸ በኋላ ክፉ ባሕርያቸውን ዘርዝሮ እግዚአብሔር ኃጢአትን ያደረጉትን መላእክት እንኳ ሳይቀር እንደቀጣቸው በመናገር ያስጠነቅቃቸዋል፡፡ በመቀጠልም ኃጢአትን በሚያደርጉት ሰዎች መካከል ጻድቅ የነበረዉ ሎጥ እንዴት እንደኖረ ይናገራል፡፡

ጻድቅ ሎጥም በመካከላቸው ሲኖር እያየና እየሰማ ዕለት ዕለት በዓመፀኛ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን አስጨንቆ ነበርና በዓመፀኞች ሴሰኛ ኑሮ የተገፋውን ያን ጻድቅ ካዳነ፥

ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን፥ በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል። ደፋሮችና ኵሩዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም፤(2ጰጥ. 2፡7-10)

ልክ እንደሎጥ በዚህ ዘመን የሚኖሩ የእግዚአብሔር ሰዎች (ቤተክርስቲያን) አስጻያፊ በሆነው የዓመፀኞች ሥራ ሳይወሰዱ በሚያድነው ጌታ በመታመን ጸንተው ሊቆሙ ይገባቸዋል፡፡ ከሚመጣውም ፍርድ ትውልድን የማዳን ኃላፊነት ከማንም በላይ የትክክለኛዋ ቤተክርስቲያን ነው፡፡

7.  የይሁዳ መልዕክት ቁ. 7

ይሁዳ ለተደራስያኑ ይህንን መልዕክት በሚጽፍበት ጊዜ የእግዚአብሔርን ጸጋ አጥላልተው የሚያስተምሩና ሥነ-ምግባር የጐደላቸው አንዳንድ መምህራን ተነስተው ነበር፡፡ በዚህ መልዕክት ተደራስያኑ እንዲጠነቀቁና የተጣመመውን ትምህርት በሚያድነው የእግዚአብሔር ጸጋና የእውነት ትምህርት ለመቃወም እንድችሉ ያሳስባቸዋል፡፡

‹‹እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል››(ይሁዳ 7)።

እንግዲህ እስካአሁን በተመለከትናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያህል ግብረሰዶማዊነትን አጥብቆ እንደሚቃወም መረዳት ችለናል ብየ አምናለሁ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን የእምነቷና የሕይወቷ መመሪያ ያደረገችው ትክክለኛዋ ቤተክርስቲያን ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ድምፅ ከፍ አድርጋ በማሰማት ትውልድንና አገርን ከአስከፊው የግብረሰዶማዊነት ከባድ ጥፋት ለመታደግ ቆርጣ ልትነሳ ይገባል፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ! ሕዝቧንም ከአስከፊው የሥነ-ምግባር ውድቀትና የግብረሰዶማዊነት ኃጢአት ይጠብቅ!! ለዛሬ አበቃሁ!

በማቴዎስ ወንጌል  5፡3 ላይ ጌታ ኢየሱስ በተራራ ላይ ሲያስተምር  በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብጹኣን ናቸው አለ፡፡ ለመሆኑ የመንፈስ ድህነት ካለብን እንዴት የእግዚአብሄር ልጆች እንባላለን? ምክንያቱም በሮሜ 8፡14 ላይ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው ይላልና፡፡ መንፈሳዊ ድህነት ካለ እንዴት የእግዚአብሄር ልጆች እንባላለን?

መልስ - በማቴዎስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 3 ላይ  እና በሮሜ 8፡14 ባሉት ጥቅሶች ላይ ተመስርተው ነው እነዚህ ሁለት ክፍሎች እንዴት ይታረቃሉ ብለው ጠያቂያችን የጠየቁት፡፡ እንደ ጥያቄያቸው ዝርዝር  የመንፈስ ድህነት ካለብን ታዲያ እንዴት የእግዚአብሔር ልጆች እንባላለን? የመንፈስ ድሀነት እንዴት ብጹዕ ያደርጋል? ጠያቂያችን እንዳሉት ማቴዎስ ምዕራፍ አምስት እስከ ምዕራፍ ሰባት ያለው ክፍል ረጅሙ የተራራው ትምህርት ተብሎ ይታወቃል ጌታ ኢየሱስ በተራራ ላይ ትምህርቱን ስለሰጠ፡፡ ይህንን ትምህርት በሚያስተምርበት ጊዜ በጊዜው የነበሩትን ውስን ደቀመዛሙርትን ብቻ እያሰበ ሳይሆን ሰፊ የሆነውን የእግዚአብሔርን አገዛዝ ወይም መንግስት መተዳደሪያ አምላክነቱንና ጌትነቱን ያኔም ሆነ ወደፊት አምነው ተከትለው የመንግስቱ ዜጎች ለሚሆኑ ሁሉ ብሎ ነው፡፡ እናም  አድማጮቹ ሰፊ ስለሆኑ ዛሬ ያለነውንም አማኞች ያካተተ ነው፡፡እናም ይሄ የህይወት የስነ ምግባር ህግ ሰዎች ምን አይነት ሥነምግባር  በምድር ሲኖሩ መከተል እንዳለባቸው የሚያሳይ የምግባር ትምህርት ነው፡፡

ይኸው ጌታ ኢየሱስ ያስተማረውን ትምህርት ስንመለከት “የመንፈስ ድህነት” የሚለውን ቃል በቀጥታ ወስደን ትርጉሙን ስንሰጥ በመንፈስ ቅዱስ ያለመመራት፣ መንፈስ ቅዱስ የሌለው መሆን እንደሆነ አያሳየንም፡፡ እዚህ ላይ መረዳት ያለብን ጠያቄያችን የጠቀሱት የሮሜው ጥቅስና ይህ ክፍል በአተረጓጎም ደረጃ አንድ ላይ የሚሄዱ አይደሉም፡፡ ጥቅሶችን ስናገናኝ አንድ ላይ እንደሚሄዱ፤ አንድ አይነት ትምህርት እንደሚሰጡ ከመጥቀሳችን በፊት እርግጠኛ መሆን አለብን፡፡ በዚህ በማቴዎስ 5 ቁጥር 3 ላይ ያለው የመንፈስ ድሀነት ሰዎች ስለራሳቸው የሚኖራቸው አመለካከት ጋር አብሮ ይሄዳል፡፡ ይህንን አስተውለን እንድንገነዘብ የሚያደርገን ነው፡፡

ጌታ ኢየሱስ ባስተማረበት እና በኖረበት ጊዜ በወቅቱ የነበሩት ፈሪሳዊያን፣ ሰዱቃዊያንና  መሰሎቻቸው የእግዚአብሔርን ህግ በማወቅ በጣም ባለጸጎች የሆኑ፣ እግዚአብሔር ላይ የደረሱ የሚመስላቸው የነበሩ ናቸው፡፡ ከሁሉም ከፍ ብለው የሚታዩ፣ በጣም አዋቂዎችና ምሁራን ነን ብለው ራሳቸውን ይቆጥሩ የነበሩ ናቸው፡፡ ከዚህ የተነሳ ትሁታን አልነበሩም፡፡ እግዚአብሔር ላይ የደረሱበት፣ ራሳቸውን በከፍታ ጫፍ ላይ ያደረሱ ይመስላቸው ነበረ፡፡ ይህንን በልባቸውና በአደባባይ የሚታየውን ማንነታቸውን ተረድቶ አጥብቆ ይቃወም የነበረው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ስለ እግዚአብሔር መንግስት ሥርዓት ሲያስተምር ሰዎች በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ሲኖሩ በውስጥ ዝንባሌያቸው ሁልጊዜ ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ፣ በእግዚአብሔር ላይ ጥገኛ በመሆን መኖር እንዳለባቸው ለማስተማር ይህንን የከበረ የብጽዕና ሥርዓት አስተማረ፡፡

ይሄ ትምህርት በውጭ እኔ ድሃ ነኝ እኔ የዋህ ነኝ ምንም አላውቅም እያሉ ነገር ግን በውስጥ የአውቃለሁ ስሜት እየተሰማን እንድንኖር ሳይሆን በውስጥ ዝንባሌ የሚሰማንን መንፈሳዊ ረሃብን፣ እግዚአብሔርን መፈለግ  እንዲኖረን የሚያስተምር ነው፡፡ ይህንን የሚያደርጉ ሰዎች በመንፈስ ድሃ ይባላሉ፡፡ ምክንያቱም እነኝህ ሰዎች በእግዚአብሔር ላይ ጥገኛና እርሱን የሚፈልጉ ናቸውና፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ፣ እግዚአብሄርን ለመጠማት መንፈሳዊ ረሃብ ምን ያህል እንደሚያስፈልግ ያመለክታል፡፡ በመንፈሳችን ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ለማወቅ የምንጠማና ያለ እርሱ እርዳታ እርሱን ማወቅ እንደማንችል አውቀን እንድንኖር የሚያሳስብ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እግዚአብሔር ለትሁታን ጸጋን ይሰጣል፣ ያሳውቃቸዋል፣ ይረዳቸዋል፣ ያሳድጋቸዋል  ስለሚል፤ በመንፈስ ድሃ መሆን ማለት ስለራሳችን ባለን አመለካከት እግዚአብሔርን ለማወቅ የምንበረታ፣ የእርሱን ነገር አውቀን ያልጨረስን፣ እግዚአብሔርን ለማወቅ ተነሳሽ የሆንን፣  ኃጢአተኛነታችንን የተረዳን፣ ያለመንፈስ ቅዱስ ዕርዳታ ምንም ነገር ማድረግ እንደማንችል ያወቅንና መንፈሳዊ ጥማት ያለን እግዚአብሔርን የምንናፍቅ እንደሆንን እያሰብን ይህንን አመለካከት ኖሮን እንድንሄድ የሚያስተምርበት ክፍል ነው፡፡  

Administrator

የሰይጣንን ፈተና እንዴት መቋቋም ይቻላል?

ብዙ ጊዜ ለፈተና የተጋለጥኩ ነኝ፤ የሥራዬም  ጸባይ ለፈተና የሚያጋልጥ ዓይነት ነው፡፡ ዘወትር በጸሎቴ ጌታ ይህንን ፈተናና ድካሜን ከኔ ያስወግድልኝ ዘንድ እጸልያለሁ ነገር ግን ምንም ልሻሻል አልቻልኩም፡፡ በመጨረሻም ምክራችሁን እጠይቅ ዘንድ ወደናንተ ጻፍኩ፡፡ ጥያቄዬ ለመሆኑ ከሰይጣንና ከእግዚአብሔር የሆኑትን ፈተናዎች የምንለየው እንዴት ነው? የሰይጣንን ፈተና መቋቋም የምችለውስ በምንድነው?

                                              ሰለሞን

                                           ከድሬዳዋ

መልስ፣ በቅድሚያ ወንድማችን ስለግልጽ ደብዳቤ እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ ደብዳቤህን አንብበን እንደተረዳነው ይህ ችግር ያንተ ብቻ ሳይሆን የብዙ ወገኖች በመሆኑና ምላሻችንም ለብዙዎች መፍትሔ ሊሆን ይችላል በማለት ሰፋ ያለ መልስ ልንሰጥ ወደድን፡፡

በጥልቅ የመከራ ሸለቆ ውስጥ ሆነን፣ የክርስትና እምነታችንን ለማጥፋት የሰይጣን ፈተናም ሆነ ወይንም ክርስቲያናዊ ባህሪያችንን ለማንጠርና ለመገንባት እያስተማረን እንደሆነ ለይተን ለማወቅ ካልቻልን ሕይወታችን ምናልባት ወደ ተሳሳተ አቅጣጫና ግምት በማዘንበል በውድቀት ላይ ውድቀት ጨምረን እጃችንን ለሰይጣን ለመስጠት እንገደዳለን፡፡

አንዲት የአንድ መጋቢ ባለቤት የሆነች እህት አንድ ቀን መሠረታዊ የሆነና ልንዘነጋው የማንችለውን ትምህርት ተናገረች፡፡ “ጠላት ሊያጠቃ በሚቃጣበት ጊዜ፣ በተከታታይ ኩነኔንና ከዛም ውስጥ መውጫ ቀዳዳ እንደሌለ አድርጎ ማወጅ ይጀምራል፡፡ ይኼኔ እኔ የማደርገው ነገር ቢኖር በኩነኔና በመናዘዝ መካከል ያለውን ልዩነት በሚገባ ማስተዋል ነው፡፡ ኩነኔን አስከትሎ የሚመጣው ነገር ቢኖር ተስፋ መቁረጥን ነው፡፡ ግን መንፈስ ቅዱስ በውስጤ ገብቶ ትክክል ባልሆንኩበት ነገር ሲወቅሰኝ ሁሌ መንገድና ተስፋ እንዳለ አምናለሁ፡፡ ወዲያውኑ በደሌን መንፈስ ቅዱስ በወቀሰኝ መሠረት እናዘዛለሁ፡፡ በኃጢዓቴም ሥርየት ተቀብዬ እነሳለሁ” በማለት ተናገረች፡፡ ድንቅና ለሕይወታችን የሚጠቅም ታላቅ ምክር እንደሆነ እናስባለን፡፡

ጠላት አሸንፎን የተወሰነውን ጎናችንን ወይንም ሙሉ በሙሉ ከሥራችን ነቅሎን በመጣል ከመንፈሳዊ ጎዳናችን ሊለየንና ሊያጠፋን ይሞክራል፡፡ እግዚአብሔርም በሌላ በኩል የእርማቱን  እርምጃ በተግሳጽ  ይገልጻል፡፡ ድካማችንንና በደላችንን ገልጾ ያሳየናል፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር ቢገስጸንና ድካማችንንም ገልጾ ቢያሳየን ታርመን መልካም ዘር በሚያድግበት ሁኔታ በእንክብካቤ እናድግ ዘንድ ነው፡፡ ይህም ስለኛ እንደሚመለከተውና ትኩረቱ ሁሉ በእኛ ላይ እንደሆነ በሚገባ ያሳየናል፡፡ እግዚአብሔር ይመክረናል እንጂ አይፈትነንም፡፡ የፈተና ሁሉ ሥር ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ በተለያየ መልኩ ይፈትነን ዘንድ ሰይጣን ወደኛ ብቅ ማለቱ አይቀርም፡፡ ለዚህ መጥፎ ተልዕኮው ቀርቦን ሊፈትነን ቢፈልግ እንኳን ብላቴናው ዮሴፍ በጶጢፋራ ቤት ሳለ ከጶጢፋራ ሚስት ለቀረበለት ፈተና “እንዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ፤ በእግዚአብሄር ፊት እንዴት ኃጢዓትን እሠራለሁ?” እንዳለው ራሳችንን በራሳችን ገስጸን መሸሽ ይኖርብናል እንጂ ቶሎ ተጣድፈን እጅ መስጠት የለብንም፡፡

አንድ ቁም ነገር እንማር ዘንድ ከጌታ የተላከ መከራ ከሆነ ደግሞ በመከራ ከምናልፈው ፈተና ልናድግበት  የምንችል ጥሩ መንፈሳዊ ልምምድን እናተርፋለን፡፡ ግን ከዚህ ውጭ ፈተናው የሰይጣን ፈተና እንደሆነ ካወቅን ዝም ብለን በጸጋው የምንቀበለው ሳይሆን የምንጋፈጠውና በጌታ ኃይል የምንዋጋው መሆን አለበት፡፡

ሰይጣን ሊዋጋን እንደሆነና ወይንም እግዚአብሄር አንድ ነገር ሊያስተምረን እንደሆነ የምንለየው በምን መንገድ ነው?

ብዙዎች በጣም የሚደናገሩበትና የሚስቱበት ጉዳይ ቢኖር ይህ ዋንኛው ነው፡፡ይህንን ጉዳይ መፍትሔ የምናገኝበት ሦስት ዓይነት መንገዶች አሉ፡፡ እነርሱም፣

  1. እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ሊናገር ይችላል፡፡ ታዲያ በዚህ በኩል እግዚአብሔር ለመናገሩ ዋና  መመዘኛው የእግዚአብሔር ድምጽ፣ ከቃሉና ከባህሪይው ጋር የማይቃረንና እጅግ ስምምነት እንዳለውና እንደሌለው ለይቶ ማወቅ ብቻ ነው፡፡
  2. አንዳንድ ድምጾች ሰይጣንን ወክለው የሚደመጡ የርኩሳን መናፍስት ድምጽ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነኝህን ከእግዚአብሔር ድምጽ መለየት አለብን፡፡
  3. አንዳንዱ ድምጽ የራሳችን የውስጣችን ድምጽ ሊሆን ይችላል፡፡ የራሳችንን የስጋ ህሊናና ተጠየቅ በመጠቀም ስሜታችንን በመከተል ከውስጣችን የሚፈልቁ ድምጾች ስላሉ፣ የራሳችንን ድምጽ ከእግዚአብሔር ድምጽ ለይተን ማወቅ አለብን፡፡

እንግዲህ ድምጾች በእነዚህ ሦስት መንገዶች ለኛ በሚደመጡበት ወቅት እኛም እነዚህን ደምጾች በመስማት የእግዚአብሄርን ድምጽ ለይተን ማወቅና መምረጥ ካቃተን የመጨረሻውም ሆነ የመጀመሪያው እርምጃችን መሆን የሚገባው መጸለይ ብቻ ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ ሰይጣን እኛን ለማሳት እጅጉን ይሞክራል፡፡ በዚህ ጊዜ የኛ ሚና መሆን ያለበት የሰይጣን ሐሳብ ወደ ልባችን፣ ወደ ህሊናችንና ወደ አካላችን ዘልቆ እንዳይገባ መቋቋም ነው፡፡ ለምሳሌ ሰይጣን ወደኛ ዘልቆ የሚገባበት መንገዶች የሚከተሉት ሲሆኑ ከነዚህ ዓይነት ድካሞች ጠንቀቅ ብለን ራሳችንን መጠበቅ ይኖርብናል፡፡

§         ከሥነ ምግባር ውጭ የሆነ ባህሪይ መታየት ሲጀምር፣ አለመታዘዝ በውስጣችን ሲያቆጠቁጥ፣ ቁጣ፣ ኩራት፣ አመጽ፣ ምህረት የለሽነትና ራስ ወዳድነት ሕይወታችንን መግዛት ሲጀምር ያኔ ሰይጣን በውስጣችን እንደዘለቀ በመረዳት፣ በፍጥነት ከውስጣችንና ከሕይወታችን ማስወገድ ይኖርብናል፡፡

§         በሰይጣን አሠራር ላይ እጅግ አላዋቂ ከሆንን በቀላሉ ወደ ተንኮሉ ወጥመድ ውስጥ ለመውደቅ ስለምንጋለጥ የሰይጣንን የተንኮል አሠራር በቅድሚያ አጢነን መረዳት ይኖርብናል፡፡

§         በእግዚአብሔር ቃልና ዓላማው ላይ ያለን ዕውቀት  እጅግ የተመጠነ ከሆነ ለክፉ ሀሳብ ተጋልጠናልና ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡

§         ከጌታ ጋር በጸሎትና በተመስጦ የምናጠፋው ጊዜ እጅግ በጣም ካነሰ፣ በዛው ልክ ራሳችንን ለሰይጣን ፈተና አጋልጠን እንደሰጠን ማወቅ ይኖርብናል፡፡

§         በጌታ ላይ ያለን አቋምና ትኩረት የማይጸናና እንደ ግራፍ የወጣና የወረደ ከሆነ፣ አሁንም ሕይወታችን ለሰይጣን የፈተና ቀስት የተጋለጠ ነውና መጠንቀቅ ይኖርብናል፡፡

§         በኤፌሶን ምዕራፍ 6 ላይ የተጠቀሱትን የመንፈሳዊ ጦር ዕቃዎችን በአግባቡ ያለመጠቀም ለሽንፈታችን ምክንያት ይሆናል፡፡

§         ዓይናችንን ከክርስቶስ ላይ አንስተን በዙሪያችን ባሉት ችግሮችና መከራዎች ላይ በምናደርግበት ጊዜ ጽናታችን ይከዳናል፣ ብርታታችን ይተወናል፡፡ ለሰይጣን ፈተናም እጃችንን ለመስጠት እንገደዳለን፡፡

§         በአካል፣ በስሜታችንም ሆነ በመንፈሳችን ላይ የሚመጣው ድካም ሌላው የሰይጣን ወደ ውስጣችን የመጥለቂያ በር ነው፡፡

§         ከቤተሰብና ከወገኖች ሕብረት መራቅም ሌላው የሰይጣን መመላለሻ መንገድ ነውና መጠንቀቁ መልካም ነው፡፡

በአጠቃላይ ምንም ጊዜ ቢሆን የመንፈሳዊ ጦርን በአግባቡ ልንጠቀም፣ ለእግዚአብሔር መታዘዛችንን ይበልጥ ልናዳብር፣ ይልቁኑ ኃጢዓትን ለመሥራት ፈቃደኛ ልብ ከሌለን በፈተና ሁሉ አሸናፊዎች ነን እንጂ ተሸናፊዎች አንሆንም፡፡ የተሰበቀብን ጦርና የተገተረብን ቀስት ይሰበራል እንጂ አይወጋንም፡፡ 

Administrator
Hiyaw Tesfa on Youtube
Find us on Facebook
Follow Us